12 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
13 ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤ለእርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤የተወሰነውም ጊዜ ደርሶአል።
14 አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤ለዐፈሯም ይሳሳሉ።
15 ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።
16 እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤በክብሩም ይገለጣል።
17 እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ልመናቸውንም አይንቅም።
18 ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤