15 ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።
16 እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤በክብሩም ይገለጣል።
17 እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ልመናቸውንም አይንቅም።
18 ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤
19 “እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቶአልና፤ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቶአል፤
20 ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”
21 ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤