18 ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤
19 “እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቶአልና፤ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቶአል፤
20 ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”
21 ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤
22 ይህም፣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣ እግዚአብሔርን ለማምለክ በአንድነት ሲሰበሰቡ ይሆናል።
23 ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤ዕድሜዬንም ባጭሩ አስቀረው።
24 እኔም እንዲህ አልሁ፤“አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ።