6 የምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጒጒት ሆንሁ።
7 ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤በቤቴ ጒልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።
8 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይዘልፉኛል፤የሚያክፋፉኝም ስሜን እንደ ርግማን ቈጥረውታል።
9 ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤መጠጤንም ከእንባ ጋር ቀላቅያለሁ።
10 ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።
11 ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።
12 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።