14 እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ትቢያ መሆናችንንም ያስባል።
15 ሰው እኮ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤እንደ ዱር አበባ ያቈጠቍጣል፤
16 ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ግን ድራሹ ይጠፋል፤ምልክቱም በቦታው አይገኝም።
17 የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤
18 ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጉት ላይ ይሆናል።
19 እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል፤መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።
20 እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክቱ፤ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኀያላን፤ እግዚአብሔርን ባርኩ።