3 ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣
4 ሕይወትሽን ከጥፋት ጒድጓድ የሚያድን፣ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣
5 ጐልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።
6 እግዚአብሔር ለተጨቈኑ ሁሉ፣ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣቸዋል።
7 መንገዱን ለሙሴ፣ሥራውንም ለእስራኤል ሕዝብ አሳወቀ።
8 እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፣ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩም የበዛ ነው።
9 እርሱ ሁል ጊዜ በደልን አይከታተልም፤ለዘላለምም አይቈጣም።