14 ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ለእንስሳት ሣርን፣ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤
15 የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል።
16 ደግሞም የእግዚአብሔር ዛፎች፣እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች ጠጥተው ይረካሉ፤
17 ወፎች ጎጆአቸውን በዚያ ይሠራሉ፤ሽመላ በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ታገኛለች።
18 ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ መኖሪያ፣የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው።
19 ጨረቃን የወቅቶች መለያ አደረግሃት፤ፀሓይም የምትጠልቅበትን ጊዜ ታውቃለች።
20 ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤የዱር አራዊትም ሁሉ በዚህ ጊዜ ወጥተው ይራወጣሉ።