2 ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል፤ሰማያትንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፤
3 የእልፍኝህን አግዳሚ በውሆች ላይ አኖርህ፤ደመናትን ሠረገላህ አደረግህ፤በነፋስ ክንፍ ትሄዳለህ።
4 መላእክትህን መንፈስ፣አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ።
5 ለዘላለም እንዳትናወጥ፣ምድርን በመሠረቷ ላይ አጸናሃት።
6 በጥልቁ እንደ ልብስ ሸፈንሃት፤ውሆችም ከተራሮች በላይ ቆሙ።
7 በገሠጽሃቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ፤የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ።
8 በተራሮች ላይ ፈሰሱ፤ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ፣ወደ ሸለቆዎች ወረዱ።