10 ይህንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ፣ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አድርጎ አጸናለት፤
11 እንዲህም አለ፤ “የርስትህ ድርሻ አድርጌ፣የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ።”
12 በቍጥር አነስተኞች ሆነው ሳሉ፣እጅግ ጥቂትና ባይተዋሮች ሳሉ፣
13 ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ሲንከራተቱ፣ከአንዱ መንግሥት ወደ ሌላው ሲቅበዘበዙ፣
14 ማንም ግፍ እንዲፈጽምባቸው አልፈቀደም፤ስለ እነርሱም ነገሥታትን እንዲህ ሲል ገሠጸ፤
15 “የቀባኋቸውን አትንኩ፤በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።”
16 በምድሪቱ ላይ ራብን ጠራ፤የምግብንም አቅርቦት ሁሉ አቋረጠ፤