11 እንዲህም አለ፤ “የርስትህ ድርሻ አድርጌ፣የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ።”
12 በቍጥር አነስተኞች ሆነው ሳሉ፣እጅግ ጥቂትና ባይተዋሮች ሳሉ፣
13 ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ሲንከራተቱ፣ከአንዱ መንግሥት ወደ ሌላው ሲቅበዘበዙ፣
14 ማንም ግፍ እንዲፈጽምባቸው አልፈቀደም፤ስለ እነርሱም ነገሥታትን እንዲህ ሲል ገሠጸ፤
15 “የቀባኋቸውን አትንኩ፤በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።”
16 በምድሪቱ ላይ ራብን ጠራ፤የምግብንም አቅርቦት ሁሉ አቋረጠ፤
17 በባርነት የተሸጠውን ሰው፣ዮሴፍን ከእነርሱ አስቀድሞ ላከ።