28 ጨለማን ልኮ ምድሪቱን ጽልመት አለበሰ፤እነርሱም በቃሉ ላይ ማመፅን ተዉ።
29 ውሃቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ዓሦቻቸውንም ፈጀ።
30 ምድራቸውም፣ የነገሥታታቸው እልፍኝ ሳይቀር፣ጓጒንቸር ተርመሰመሰባቸው።
31 እርሱ በተናገረ ጊዜ የዝንብ መንጋ መጣ፤ትንኞችም ምድራቸውን ወረሩ።
32 ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፤ምድራቸውም ሁሉ መብረቅ አወረደ።
33 ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፤የአገራቸውንም ዛፍ ከተከተ።
34 እርሱ በተናገረ ጊዜ አንበጣ መጣ፤ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ ከተፍ አለ፤