1 ሃሌ ሉያቸር ነውና፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ምሕረቱም ለዘላለም ነውና።
2 ስለ እግዚአብሔር ታላቅ ሥራ ማን ሊናገር ይችላል?ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ተናግሮ ይጨርሳል?
3 ፍትሕ እንዳይዛነፍ የሚጠብቁ፣ጽድቅን ሁል ጊዜ የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ ለሕዝብህ ሞገስ ስታድል አስበኝ፤በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፤