2 ስለ እግዚአብሔር ታላቅ ሥራ ማን ሊናገር ይችላል?ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ተናግሮ ይጨርሳል?
3 ፍትሕ እንዳይዛነፍ የሚጠብቁ፣ጽድቅን ሁል ጊዜ የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ ለሕዝብህ ሞገስ ስታድል አስበኝ፤በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፤
5 ይኸውም የምርጦችህን ብልጽግና አይ ዘንድ፣በሕዝብህ ደስታ ደስ ይለኝ ዘንድ፣ከርስትህም ክብር የተነሣ እጓደድ ዘንድ ነው።
6 እኛም እንደ አባቶቻችን ኀጢአት ሠራን፤በደልን፤ ክፉም አደረግን።
7 አባቶቻችን በግብፅ ሳሉ፣ታምራትህን አላስተዋሉም፤የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ።
8 እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ስለ ስሙ አዳናቸው።