26 በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣እጁን አንሥቶ ማለ፤
27 ዘራቸውንም በሕዝቦች መካከል ሊጥል፣ወደ ተለያየ ምድርም እንደሚበትናቸው ማለ።
28 ራሳቸውን ከብዔል ፌጎር ጋር አቈራኙ፤ለሙታን የተሠዋውን መሥዋዕት በሉ፤
29 በሥራቸውም እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ቸነፈርም በላያቸው መጣ።
30 ፊንሐስም ተነሥቶ ጣልቃ ገባ፤ቸነፈሩም ተገታ፤
31 ይህም ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ለዘላለም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።
32 ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ሙሴም ከእነርሱ የተነሣ ተቸገረ፤