40 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ርስቱንም ተጸየፈ።
41 ለአሕዛብ አሳልፎ ሰጣቸው፤ጠላቶቻቸውም በላያቸው ሠለጠኑ።
42 ጠላቶቻቸው ጨቈኗቸው፤በሥልጣናቸውም ሥር አዋሏቸው።
43 እርሱ ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤እነርሱ ግን ዐመፃን የሙጥኝ አሉ፤በኀጢአታቸውም ተዋረዱ።
44 ሆኖም ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ፣ጭንቀታቸውን ተመለከተ፤
45 ለእነርሱም ሲል ቃል ኪዳኑን አሰበ፤እንደ ምሕረቱም ብዛት ከቍጣው ተመለሰ።
46 የማረኳቸው ሁሉ፣እንዲራሩላቸው አደረገ።