6 እኛም እንደ አባቶቻችን ኀጢአት ሠራን፤በደልን፤ ክፉም አደረግን።
7 አባቶቻችን በግብፅ ሳሉ፣ታምራትህን አላስተዋሉም፤የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ።
8 እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ስለ ስሙ አዳናቸው።
9 ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው።
10 ከባለጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ከጠላትም እጅ ታደጋቸው።
11 ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ከእነርሱም አንድ አልተረፈም።
12 ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤በዝማሬም አመሰገኑት።