8 እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ስለ ስሙ አዳናቸው።
9 ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው።
10 ከባለጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ከጠላትም እጅ ታደጋቸው።
11 ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ከእነርሱም አንድ አልተረፈም።
12 ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤በዝማሬም አመሰገኑት።
13 ነገር ግን ያደረገውን ወዲያውኑ ረሱ፤በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም።
14 በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።