1 ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ምሕረቱም ለዘላለም ነውና።
2 እግዚአብሔር የተቤዣቸው፣ከጠላት እጅ የታደጋቸው ይህን ይበሉ፤
3 ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ፣ከየአገሩ የሰበሰባቸው እንዲህ ይናገሩ።
4 አንዳንዶቹ ጭው ባለ በረሓ ተቅበዘበዙ፤ወደሚኖሩባት ከተማ የሚያደርስ መንገድ አጡ።
5 ተራቡ፤ ተጠሙ፤ነፍሳቸውም በውስጣቸው ዛለች።