22 የምስጋናም መሥዋዕት ያቅርቡለት፤ሥራውንም ደስ በሚል ዝማሬ ይግለጹ።
23 አንዳንዶቹ በመርከብ ወደ ባሕር ወረዱ፤በታላቅም ውሃ ላይ ሥራቸውን አከናወኑ፤
24 የእግዚአብሔርን ሥራ በዚያ አዩ፤ድንቅ አድራጎቱንም በጥልቁ ውስጥ ተመለከቱ።
25 እርሱ ተናግሮ ዐውሎ ነፋስን አስነሣ፤ነፋሱም ማዕበሉን ከፍ ከፍ አደረገ።
26 ወደ ሰማይ ወጡ፤ ወደ ጥልቅም ወረዱ፤ከመከራቸውም የተነሣ ሐሞታቸው ፈሰሰ።
27 እንደ ሰከረ ሰው ዞሮባቸው ወዲያ ወዲህ ተንገዳገዱ፤መላው ጠፍቶባቸው የሚያደርጉትን አጡ።
28 በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።