28 በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።
29 ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ፤የባሕሩም ሞገድ ረጭ አለ።
30 ጸጥ በማለቱም ደስ አላቸው፤ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው።
31 እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤
32 በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤በሽማግሌዎችም ሸንጎ ይወድሱት።
33 ወንዞችን ወደ ምድረ በዳ፣የውሃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ ምድር ለወጠ።
34 ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ፍሬያማዋን ምድር በጨው የተበከለች አደረጋት።