35 ምድረ በዳውን ወደ ውሃ መከማቻ፣ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ።
36 የተራቡትን በዚያ አስቀመጠ፤የሚኖሩባትንም ከተማ ሠሩ።
37 በዕርሻውም ዘሩበት፤ ወይንም ተከሉ፤ብዙ ፍሬም አመረቱ።
38 ይባርካቸዋል፤ እነርሱም እጅግ ይበዛሉ፤የከብቶቻቸውም ብዛት እንዲያንስ አያደርግም።
39 በጭንቅ፣ በመከራና በሐዘን፣ቍጥራቸው አንሶ፣ ተዋርደው ነበር፤
40 በመኳንንቱም ላይ መናቅን አዘነበባቸው፤መውጫ መግቢያው በማይታወቅ በረሓ ውስጥም አንከራተታቸው።
41 ችግረኞችን ግን ከጭንቀታቸው መዝዞ አወጣቸው፤ቤተ ሰባቸውንም እንደ በግ መንጋ አበዛ።