5 ተራቡ፤ ተጠሙ፤ነፍሳቸውም በውስጣቸው ዛለች።
6 በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።
7 ወደሚኖሩባትም ከተማ፣በቀና መንገድ መራቸው።
8 እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤
9 እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቶአልና፤የተራበችውንም ነፍስ በበጎ ነገር አጥግቦአል።
10 አንዳንዶቹ በብረት ሰንሰለት ታስረው የተጨነቁ፣በጨለማ፣ በጥልማሞት ውስጥ የተቀመጡ ነበሩ፤
11 በእግዚአብሔር ቃል ላይ በማመፅ፣የልዑልን ምክር አቃለዋልና።