4 ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና፤ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ትደርሳለች።
5 አምላክ ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።
6 ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣በቀኝ እጅህ ታደግ፤ መልስልኝም።
7 እግዚአብሔር ከመቅደሱ እንዲህ አለ፤ደስ እያለኝ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤“የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።
8 ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ይሁዳም በትረ መንግሥቴ።
9 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እፎክራለሁ።”
10 ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?ወደ ኤዶምያስስ ማን ያደርሰኛል?