21 አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ስለ ስምህ በበጎ ተመልከተኝ፤ምሕረትህም መልካም ናትና አድነኝ።
22 እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ልቤም በውስጤ ቈስሎአልና።
23 እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ።
24 ከጾም የተነሣ ጒልበቴ ዛለ፤ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ ለበሰ።
25 ለመሣለቂያ ሆንሁላቸው፤ሲያዩኝም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።
26 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤እንደ ምሕረትህም አድነኝ።
27 እግዚአብሔር ሆይ፤ እጅህ ይህን እንዳደረገች፣አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ።