23 እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ።
24 ከጾም የተነሣ ጒልበቴ ዛለ፤ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ ለበሰ።
25 ለመሣለቂያ ሆንሁላቸው፤ሲያዩኝም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።
26 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤እንደ ምሕረትህም አድነኝ።
27 እግዚአብሔር ሆይ፤ እጅህ ይህን እንዳደረገች፣አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ።
28 እነርሱ ይራገማሉ፤ አንተ ግን ትባርካለህ፤በሚነሡበት ጊዜ ይዋረዳሉ፤ባሪያህ ግን ሐሤት ያደርጋል።
29 የሚወነጅሉኝ ውርደትን ይከናነቡ፤ዕፍረትንም እንደ ሸማ ይልበሱ።