4 ስወዳቸው ይወነጅሉኛል፤እኔ ግን እጸልያለሁ።
5 በበጎ ፈንታ ክፋትን፣በወደድኋቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል።
6 ክፉ ሰው በላዩ ሹም፤ከሳሽም በቀኙ ይቁም።
7 ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ ሆኖ ይገኝ፤ጸሎቱም ለፍርድ ትሁንበት።
8 ዕድሜው ይጠር፤ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው።
9 ልጆቹ ድኻ አደጎች ይሁኑ፤ሚስቱም መበለት ትሁን።
10 ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ፤ከፈረሰው ቤታቸውም ይሰደዱ።