1 እግዚአብሔር ጌታዬን፣“ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ፣እስከማደርግልህ ድረስ፣በቀኜ ተቀመጥ” አለው።
2 እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰዳል፤አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።
3 ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ከንጋት ማሕፀን፣በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣የጐልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።
4 “እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት፤አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣ እግዚአብሔር ምሎአል፤እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።
5 ጌታ በቀኝህ ነው፤በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቃቸዋል።