6 ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣የአሠራሩን ብርታት አሳይቶአል።
7 የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው፤ሥርዐቱም ሁሉ የታመነ ነው፤
8 ከዘላለም እስከ ለዘላለም የጸና ነው፤በእውነትና በቅንነትም የተሠራ ነው።
9 ለሕዝቡ መዳንን ሰደደ፤ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ፤ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው።
10 እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።