2 ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
3 ሀብትና ብልጽግና በቤቱ ይሞላል፤ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።
4 ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።
5 ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል፤
6 ለዘላለም ከስፍራው አይናወጥምና፤ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል።
7 ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።
8 ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።