7 ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።
8 ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።
9 በልግስና ለድኾች ሰጠ፤ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
10 ክፉ ሰው ይህን በማየት ይበሳጫል፤ጥርሱን ያፋጫል፤ እየመነመነም ይጠፋል፤የክፉዎችም ምኞት ትጠፋለች።