1 ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤ የእግዚአብሔርን ስም አወድሱ።
2 ከአሁን እስከ ዘላለም፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
3 ከፀሓይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
4 እግዚአብሔር ከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።
5 እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር፣በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?
6 በሰማይና በምድር ያሉትንስ ለማየት፣ራሱን ወደ ታች ዝቅ የሚያደርግ ማን ነው?
7 ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤