1 ለእኛ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለእኛ ሳይሆን፣ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ፣ለስምህ ክብርን ስጥ።
2 አሕዛብ፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?
3 አምላካችንስ በሰማይ ነው፤እርሱ ደስ የሚለውን ያደርጋል።
4 የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ የሠራቸው፣ብርና ወርቅ ናቸው።
5 አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤ዐይን አላቸው፤ አያዩም፣
6 ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤አፍንጫ አላቸው፤ አያሸቱም፤