12 እግዚአብሔር ያስበናል፤ ይባርከናልም፤እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤የአሮንንም ቤት ይባርካል።
13 እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሁሉ፣ትልቁንም ትንሹንም ይባርካል።
14 እግዚአብሔር እናንተንና ልጆቻችሁን፣በባርኮቱ ያብዛችሁ።
15 ሰማይንና ምድርን በፈጠረ፣ በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ሁኑ።
16 ሰማየ ሰማያት የእግዚአብሔር ናቸው፤ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።
17 እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑት የሞቱት አይደሉም፤ወደ ዝምታው ዓለም የሚወርዱም አይደሉም።
18 ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ እግዚአብሔርን የምንባርክ እኛ ነን። እግዚአብሔር ይመስገን።