3 አምላካችንስ በሰማይ ነው፤እርሱ ደስ የሚለውን ያደርጋል።
4 የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ የሠራቸው፣ብርና ወርቅ ናቸው።
5 አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤ዐይን አላቸው፤ አያዩም፣
6 ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤አፍንጫ አላቸው፤ አያሸቱም፤
7 እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤በጒሮሮአቸውም ድምፅ አይፈጥሩም።
8 እነዚህን የሚያበጁ፣የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
9 የእስራኤል ቤት ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።