1 የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት።
2 ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና፣በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።
3 የሞት ወጥመድ ያዘኝ፤የሲኦልም ጣር አገኘኝ፤ጭንቅና ሐዘን አሸነፈኝ።
4 እኔም የእግዚአብሔርን ስም ጠራሁ፤“እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እለምንሃለሁ” አልሁ።
5 እግዚአብሔር ቸርና ጻድቅ ነው፤አምላካችን መሓሪ ነው።