12 ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?
13 የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።
15 የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።
16 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፣ከእስራቴም ፈታኸኝ።
17 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
18 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤