6 እግዚአብሔር ገሮችን ይጠብቃል፤እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ።
7 ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና፤
8 አንተ ነፍሴን ከሞት፣ዐይኔን ከእንባ፣እግሮቼን ከመሰናከል አድነሃልና።
9 እኔም በሕያዋን ምድር፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።
10 “እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣እምነቴን ጠብቄአለሁ።
11 ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣“ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።
12 ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?