1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ደግ ሰው የለምና አንተው ድረስልኝ!ከሰዎችም መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም።
2 እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ፤
3 ሸንጋዩን ከንፈር ሁሉ፣ነገር የምታበዛውንም ምላስ እግዚአብሔር ያጥፋ!
4 እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤ከንፈራችን የእኛ ነው፤ ጌታችንስ ማነው?”የሚሉ ናቸው።