1 ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል?
2 ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።
3 እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤የሚጠብቅህም አይተኛም።
4 እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ፣ አይተኛም፤ አያንቀላፋምም።