1 በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጥህ ሆይ፤ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣለሁ።
2 የባሪያዎች ዐይን ወደ ጌታቸው እጅ፣የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት፣ምሕረት እስከሚያደርግልን ድረስ፣የእኛም ዐይኖች ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለከታሉ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ንቀት በዝቶብናልና፣ማረን፣ እባክህ ማረን።
4 ነፍሳችን የቅንጡዎች ስድብ፣የትዕቢተኞችም ንቀት እጅግ በዝቶባታል።