2 በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣እንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣“እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
3 እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤እኛም ደስ አለን።
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ በነጌቭ እንዳሉ ጅረቶች፣ምርኳችንን መልስ።
5 በእንባ የሚዘሩ፣በእልልታ ያጭዳሉ።
6 ዘር ቋጥረው፣እያለቀሱ የተሰማሩ፣ነዶአቸውን ተሸክመው፣እልል እያሉ ይመለሳሉ።