1 እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ?ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ድረስ ነው?
2 ከሐሳቤ ጋር የምሟገተው፣ልቤም ቀኑን ሙሉ የሚያዝነው እስከ መቼ ነው?ጠላቴስ በእኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ድረስ ነው?
3 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤ስማኝም፤የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤
4 በዚህም ጠላቴ፣ “አሸነፍሁት” እንዳይል፣ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ።
5 እኔ ግን በጸናች ፍቅርህ እታመናለሁ፤ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።