3 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤ስማኝም፤የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤
4 በዚህም ጠላቴ፣ “አሸነፍሁት” እንዳይል፣ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ።
5 እኔ ግን በጸናች ፍቅርህ እታመናለሁ፤ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
6 ቸርነቱ በዝቶልኛልና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።