1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ።
2 ጌታ ሆይ፤ ድምፄን ስማ፤ጆሮዎችህ የልመናዬን ቃል፣የሚያዳምጡ ይሁኑ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአትን ብትቈጣጠር፣ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል?
4 ነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ፤ስለዚህም ልትፈራ ይገባሃል።