2 ጌታ ሆይ፤ ድምፄን ስማ፤ጆሮዎችህ የልመናዬን ቃል፣የሚያዳምጡ ይሁኑ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአትን ብትቈጣጠር፣ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል?
4 ነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ፤ስለዚህም ልትፈራ ይገባሃል።
5 እግዚአብሔርን ደጅ እጠናለሁ፤ ነፍሴም በትዕግሥት ትጠብቀዋለች፤በቃሉም ተስፋ አደርጋለሁ።
6 ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣አዎን፤ ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ነፍሴ ጌታን ትጠባበቃለች።
7 በእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት፣በእርሱም ዘንድ ማዳን አለና፣እስራኤል ሆይ፤ በእግዚአብሔር ተስፋ አድርግ።
8 እርሱም እስራኤልን፣ከኀጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።