1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ዳዊትን፣የታገሠውንም መከራ ሁሉ ዐስብ፤
2 እርሱ ለእግዚአብሔር ማለ፤ለያዕቆብም ኀያል አምላክ እንዲህ ሲል ተሳለ፤
3 “ወደ ቤቴ አልገባም፤ዐልጋዬም ላይ አልወጣም፤
4 ለዐይኖቼ እንቅልፍን፣ለሽፋሽፍቶቼም ሸለብታ አልሰጥም፤
5 ለእግዚአብሔር ስፍራን፣ለያዕቆብም ኀያል አምላክ ማደሪያን እስካገኝ ድረስ።”
6 እነሆ፤ በኤፍራታ ሰማነው፤በቂርያትይዓሪም አገኘነው።
7 “ወደ ማደሪያው እንግባ፤እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።