14 “ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ፈልጌአታለሁና በእርሷ እኖራለሁ።
15 እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ፤ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ።
16 ለካህናቷ ድነትን አለብሳለሁ፤ቅዱሳኗም በደስታ ይዘምራሉ።
17 “በዚህም ለዳዊት ቀንድ አበቅላለሁ፤ለቀባሁትም ሰው መብራት አዘጋጃለሁ።
18 ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባቸዋለሁ፤እርሱ ግን በራሱ ላይ የደፋው ዘውድ ያበራል።