4 ለዐይኖቼ እንቅልፍን፣ለሽፋሽፍቶቼም ሸለብታ አልሰጥም፤
5 ለእግዚአብሔር ስፍራን፣ለያዕቆብም ኀያል አምላክ ማደሪያን እስካገኝ ድረስ።”
6 እነሆ፤ በኤፍራታ ሰማነው፤በቂርያትይዓሪም አገኘነው።
7 “ወደ ማደሪያው እንግባ፤እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ፤አንተና የኀይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ሂዱ።
9 ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”
10 ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል፣የቀባኸውን ሰው አትተወው።