1 ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርን ስም ወድሱ፤እናንት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤
2 በእግዚአብሔር ቤት፣በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት።
3 እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤መልካም ነውና፣ ለስሙ ዘምሩ፤
4 እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፣እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጦአልና።
5 እግዚአብሔር ታላቅ እንደሆነ፣ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና።