14 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳልና፣ለአገልጋዮቹም ይራራላቸዋል።
15 የአሕዛብ ጣዖታት ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣የሰው እጅ ያበጃቸው ናቸው።
16 አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤ዐይን አላቸው፤ አያዩም፤
17 ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤በአፋቸውም እስትንፋስ የለም።
18 እነዚህን የሚያበጁ፣የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
19 የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ፤የአሮን ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ፤
20 የሌዊ ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ፤ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ።